እርስዎ ወይም ጓደኛዎት በግዴታ ጋብቻ ላይ ከሆኑ ወይም በግዴታ ስለማግባት የሚያሳስብዎት ሁኔታ ላይ ከሆኑ፤ እባክዎን ለዚህ እርዳታ እንደሚቀርብና ብቻዎን እንዳልሆኑም ይወቁ።
በወደፊት ሁኔታ ላይ ሊያስፈራዎትና እርግጠኛ ላለመሆን ሲችሉ፤ እንዱሁም ስለርስዎ ስሜትና ተግባራት ሊደናገሩ ይችላሉ። በዚህ ገጽ ላይ ባሉት የስልክ ቁጥሮች ላይ አንደኛውን በማነጋገር እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።
የርስዎ እድሜ ምን ያህል ይሁን፤ ከየትም አገር ወይም ቤተሰብ ይምጡ፤ ወንድም ሆኑ ሴት ጾታ፤ ወይም ከየትም ባህላዊ ወይም ሃይማኖት ቢመጡም – አንድ ሰው ከፍላጎቱ ውጭ በግዴታ ጋብቻ እንዲፈጽም ለማድረግ ማንም ሰው አይፈቀድለትም።