ሆም ፔጅ

በግዴታ ጋብቻ ላይ ከሆኑ ወይም በግዴታ ስለማግባት የሚያሳስብዎት ከሆነ፤ እባክዎን ለዚህ እርዳታ እንደሚቀርብና ብቻዎን እንዳልሆኑም ይወቁ።

በወደፊት ሁኔታ ላይ ሊያስፈራዎትና እርግጠኛ ላለመሆን ሲችሉ፤ እንዱሁም ስለርስዎ ስሜትና ተግባራት ሊደናገሩ ይችላሉ። በዚህ ገጽ ላይ ባሉት የስልክ ቁጥሮች ላይ አንደኛውን በማነጋገር እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።

የርስዎ እድሜ ምን ያህል ይሁን፤ ከየትም አገር ወይም ቤተሰብ ይምጡ፤ ወንድም ሆኑ ሴት ጾታ፤ ወይም ከየትም ባህላዊ ወይም ሃይማኖት ቢመጡም አንድ ሰው ከፍላጎቱ ውጭ በግዴታ ጋብቻ እንዲፈጽም ለማድረግ ማንም ሰው አይፈቀድለትም።

ምክር ከፈለጉ፤ በስልክ (02) 9514 8115 አድርጎ መደወል ወይም በኢሜል፡help@mybluesky.org.au መላክ ወይምበተክስት ቁጥር 0481 070 844 አድርጎመልእክት መላክ ነው። ከአስተጓሚእርዳታ ጋር እንድንረዳዎ ከፈለጉማቀናጀት እንችላለን።

የደህንነት ስሜት ከሌለ? ድንገተኛ ችግር ወይም ጉዳት ከደረሰብዎ ከማንኛውም ስልክ ላይ ሆኖ በሶስት ዜሮ (000) አስድጎ መደወል።

በግዲታ ጋብቻ ምንድ ነው?

አንድ ሰው በጋብቻ ስነስርዓት መፈጸም ላይ ነጻ ሆኖ ሙሉ ስምምነት ሳያደርግ የግዳጅ ጋብቻ ይባላል የዚህም ምክንያት ጋብቻው ሲፈጸም ያለውን ሁኔታና ስለሚከሰት ችግር  ሳይረዳው ወይም በግዳጅ፣ በማስፈራራት ወይም በማታለል የሆነ ሰው እንዲያገባ ማደርግ ነው። በዚህ ላይ ሊካተት የሚችለው ከእነሱ ቤተሰብ ወይም ማህበረሰብ ስሜታዊ ግፊት፤ ማስፈራራት፤ የአካል ጉዳት፤ ወይም የሆነን ሰው ለማግባት ማታለል ይሆናል። የዚህ ዓይነቱ ጋብቻ በሰዎችና በቤተሰቦች ላይ የረጅም ጊዜ አንጻራዊ ችግር ሊፈጥር እንደሚችልና በአውስትራሊያ ውስጥ ህገ-ወጥነት ነው።

ስለ ግዴታ ጋብቻ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ባለው ተጭኖ ማውጣት።

Banner
Locker Room

The Locker Room

Close