በግዳጅ ጋብቻ ምንድ ነው?

በግዴታ ጋብቻ ምንድ ነው?

በግዴታ ጋብቻ ላይ ከሆኑ ወይም በግዴታ ስለማግባት የሚያሳስብዎት ከመሆነ፤ እባክዎን ለዚህ እርዳታ እንደሚቀርብና ብቻዎን እንዳልሆኑ ይወቁ። በወደፊት ሁኔታ ላይ ሊያስፈራዎትና እርግጠኛ ላለመሆን ሲችሉ፤ እንዱሁም ስለርስዎ ስሜትና ተግባራት ሊደናገሩ እንደሚችሉና በቀጣዩ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ላለማወቅ ይችላሉ። በዚህ ገጽ ላይ ባሉት የስልክ ቁጥሮች ላይ አንደኛውን በማነጋገር አንዳንድ እርዳታና ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

አንድ ሰው በጋብቻ ስነስርዓት መፈጸም ላይ ነጻ ሆኖ ሙሉ ስምምነት ሳያደርግ የግዳጅ ጋብቻ ይባላል። የዚህም ምክንያት ጋብቻው ሲፈጸም ያለውን ሁኔታና ስለሚከሰት ችግር  ሳይረዳው ወይም በግዳጅ፣ በማስፈራራት ወይም በማታለል የሆነ ሰው እንዲያገባ ማደርግ ነው። በዚህ ላይ ሊካተት የሚችለው ከእነሱ ቤተሰብ ወይም ማህበረሰብ ስሜታዊ ግፊት፤ ማስፈራራት፤ የአካል ጉዳት፤ ወይም የሆነን ሰው ለማግባት ማታለል ይሆናል። የዚህ ዓይነቱ ጋብቻ በሰዎችና በቤተሰቦች ላይ የረጅም ጊዜ አንጻራዊ ችግር ሊፈጥር እንደሚችልና በአውስትራሊያ ውስጥ ህገ-ወጥነት ነው።


በአውስትራሊያ ውስጥ ስላለው ህግ የመረጃ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

በአውስትራሊያ ውስጥ በግዴታ ጋብቻ ህገወጥ እንደሆነ መጋቢት/March 2013 ዓ.ም ተግባራዊ የሆነ ህግ ወጥቷል። አንድን ሰው (እርስዎ ተበዳዩ ካልሆኑ በስተቀር) በግዴታ ጋብቻ ላይ እንዲገባ ምክንያት መሆን ወይም ለግዴታ ጋብቻ ተሳታፊ መሆን ወንጀል ነው። ይህ ህግ በክፍል/Division 270 የኮመንዎልዝ ወንጀለኛ ደንብአንቀጽ ህግ 1995/ Commonwealth Criminal Code Act 1995 ዓ.ም ውስጥ ይካተታል። በዚህ የማገፋፋት ወንጀል ፍጸማ በከፍተኛ እስከ 7 ዓመታት ወይም 9 ዓመታት እስራት እንዳለው፤ ይህም እድሜው ከ18 ዓመት ለሆነ ሰው በግዴታ ለማጋባት ወይም ከአካለ ጉዳተኛ ሰው ጋር ለማጋባት ማስገደድን ያካትታል። እድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነን ህጻን ለማጋባት ከውስትራሊያ ውጭ ለመውስድ የሆነ ሰው ከረዳ እስከ 25ዓመታት እስር ቤት ሊገባ ይችላል።


በግዴታ ጋብቻ ላይ ከሆኑ

… ወይም በግዴታ ጋብቻ አደርጋለሁ በሚል የሚጨነቁ ከሆነ፤ እባክዎ ለዚህ እርዳታ እንደሚቀርብና ብቻዎን እንዳልሆኑ ይወቁ። በወደፊት ሁኔታ ላይ ሊያስፈራዎትና እርግጠኛ ላለመሆን ይችላሉ። እንዱሁም ስለርስዎ ስሜትና ተግባራት ሊደናገሩ እንደሚችሉና በቀጣዩ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ላለማወቅ ይችላሉ። በዚህ ገጽ ላይ ባሉት የስልክ ቁጥሮች ላይ አንደኛውን በማነጋገር አንዳንድ እርዳታና ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

ለግዴታ ጋብቻ ፍጻሜ ምሳሌ

1. “ 17-ዓመትእድሜ ልጃገረድ የወንድ ጓደኛ አላት ነገር ግን ወላጆቿ እሱን ከማየት እንድታቋርጥና ሌላ ሰው እንድታገባ ነገሯት። እንደተነገራት፤ ሌላውን ሰውየ ለማግባት የማትስማማ ከሆነ ጉዳት እንደሚደርስባት ነው። ልጃገረዷ ጉዳት ይደርስብኛል በሚል የፍርሃት ምክንያት በጋብቻው ከቀጠለችበት፤ ይህ የግዴታ ጋብቻ ይባላል።

ለግዴታ ጋብቻ ፍጻሜ ምሳሌ

2. “15-ዓመትእድሜ ልጃገረድበትምህርት ቤት እረፍት ጊዜ ከቤተሰብ ጋር እረፍት ለማድረግ እንደምትሄድ ይነገራታል። እርሷና ቤተሰቧ በውጭ አገር ሲደርሱ፤ የአጎት/አክስት ልጅን ማግባት እንዳለባት ይነገራታል። በዚህ ጋብቻ ላይ ካልተስማማች ወደ አውስትራሊያ በምንም መመለስ እንደማትችል ይነገራታል። ጋብቻው ከተፈጸመ ይህ የግዴታ ጋብቻ ይባላል

ለግዴታ ጋብቻ ፍጻሜ ምሳሌ

3. “19-ዓመትr-እድሜ ወንድ ሰው ግብረ ሶዶማዊ እንደሆነ ለቤተሰቡ ይናገራል ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በማህበረሰቡ ውስጥ ለብዙ ዓመታት የሚያውቃትን ወጣት ሴት ልጅ ማግባት እንዳለበት ቤተሰቡ ይነግሩታል። ጋብቻው ቀጠለ ምክንያቱም እሷን ካላገባ ለቤተሰቡ ብዙ ሃፍረትን እንደሚፈጥርና በሴት አያቱ የልብ ህመም ሊፈጠር ስለሚችል ስለተነገረው ነው። ይህ የግዴታ ጋብቻ ይባላል

የቅንጅት ጋብቻ ምንድ ነው?

በአንዳንድ ቤተሰቦት ጋብቻ በተቀናጀ መልኩ ይሆናል። ሁለቱም ጥንዶች በቤተሰብ አባል ወይም በሌላ ሰው በኩል ይተዋወቃሉ። በጋብቻው ላይ መቀጠል ወይም ላለመቀጠል ፍላጎት እያንዳንዱ ግለሰብ ለመምረጥ ነጻ ሲሆን ወላጆች ያለምንም ተጽእኖ ያላቸውን ምርጫ ያዳምጣሉ። በአውስትራሊያ ውስጥ እድሚያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች የቅንጅት ጋብቻ ህጋዊ ሲሆን ምክንያቱም ሁለቱም ጥንዶች ጋብቻ ለመፈጸም በራሳቸው ነጻ በሆነ ምርጫ ብቻ በመሆኑ ነው።

ምንም እንኳን በመጀመሪያ ለቅንጅት ጋብቻው ቢስማሙም፤ ይህ የቅንጅት ጋብቻ ወደ የግዴታዊ ጋብቻ ሊቀየር ይችላል፤ ይህም ለጋብቻው አዎ ለማለት በአንዳቸው ወይም በሁለቱ ላይ የማስፈራራት፤ ማጭበርበር ወይም ግፊት ካለባቸው ይሆናል። ለሰርጉ እምቢ ማለቱ ሰውየው አይረዳም የሚል ስሜት ሊያድርበት ይችላል። በዚያን ጊዜ ሙሉና ነጻ የሆነ ስምምነት እንዳልሰጡ ሲሆን ታዲያ ጋብቻው ወደ ግዴታ ጋብቻ እንደሚቀየር ነው።

ለቅንጅት ጋብቻ ምሳሌ እዚህ ላይ ይጫኑ

19-ዓመትእድሜ ግለሰብ በቤተሰብ አባል፤ ጓደኛ ወይም ሌላ ሶስተኛ አካል በኩል ለወደፊት ጋብቻ ጥንድ የሚሆን ሰው ይተዋወቃል። ግለሰቡ ለጋብቻው እሺወይምእምቢለማለት መምረጥ ይችላል። እምቢለማለት ከወሰኑ በቀላሉ ሁኔታው ለወደፊት አይቀጥልም። ለጋብቻው በራሳቸው ሙሉና ነጻ ስምምነት አዎማለት ከወሰኑ፤ ጋብቻው ወደፊት ይቀጥላል። የእነሱ ሙሉና ነጻ ስምምነት ማለት ለጋብቻው እሺ ለማለት ምንም የማስፈራራት፤ ማጭበርበር ወይም ግፊት በነሱ ላይ እንዳልነበረ ነው።

Banner

በኮምፑውተርና ስልክ ደህንነት

ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ላይ ሆኖ ድህንነቱ የተጠበቀን ስልክ ወይም ኮምፑውተር ስለመጠቀምያረጋግጡ፤ ስለዚህ ማንም ሊከታተልዎት ወይም ሊያጭበረብርዎት አይችልም። ለደህንነትዎ የሚጨነቁ ከሆነ የርስዎን ጓደኛ ሞባይል ስልክ መዋስ ይችላሉ ወይም በህዝባዊ ቤተመጽሐፍ ወይም በማህበረሰብ ማእከል ባለው ኮምፑውተር ላይ መጠቀም።

ከዚህ ድረገጽ ላይ በተሎ ለመውጣት ከፈለጉ፤ በዚህ ገጽ ቀኝ ጫፍ ባለውከድረገጽ መውጣትየሚለውን ቁልፍ መጫን። ይህ በቀጥታ ወደ ክፍት ጎግል/Google መፈለጊያ ገጽ ሲወስድዎት ነገር ግን ያለዎትን የመፈለጊያ/ browser ታሪክ አይጠፋም።

Locker Room

The Locker Room

Close